Posts

ትንሳኤ

        " ተነስቷል "    የተናገረውን የሚያደርግ የማያደርገውን የማይናገር በቃልም በግብርም የታመነው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀድሞ በገነት የሳተውን አዳምን እና በአዳም ውድቀት የወደቅነውን እኛ ሁላችንን ያጣናትን ሰማያዊት አገራችንን ሊመልስልን ከገባንበት ጨለማና ፍርድ ሊቤዠን የተናገራትን ቀን ቆጥሮ ተገለጠልን ።  በነገራችን ላይ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣው ለመሞት ነው ። ደም ሳይፈስስ ሰርየት የለም እንዳለው መጽሃፍ የእንስሳት እና የሰዎች ደም በክርስቶስ የመጣውን ስር ነቀል ለውጥ ሊያመጣ ስላልቻለ ደግሞም ስለማይችል በመስቀል ላይ ሃጢአታችንን ሊሸከም ፣ሞቶ ሞትን ሊገድል ፣በትንሳኤውም ዘለዓለማዊነታችንን ሊያረጋግጥልን በኩር ሆነልን ።     ስለዚህ የመጣበትን አላማ ስለሚያውቅ ብዙ ውርደት በትህትና ተቀበለ ብዙ ስቃይ በዝምታ አስተናገደ መከራውን ሳይሆን በመከራው የምንተርፈውን የእኛን መዳን እያየ ተፅናና በችንካር እያማጠ ዳግመኛ ከማይጠፋ ዘር  ወለደን።      በሚያስተምርበት ወቅት ይህንን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሶስተኛውም ቀን አነሳዋለሁ እንዳለው ሶስት ቀንና ሶስት ሌሊት በምድር ውስጥ አሳልፎ በሶስተኛው ቀን የሞትን ሃይል አድቅቆ የመቃብርን ህግ ሽሮ ዳግም በማይሞት ማንነት እና አካል በተዘጋ መቃብር ኢየሱስ ተነሳ። ክብር ምስጋና ኃይልና ስልጣን ሁሉ ለእርሱ ይሁን አሜን ።    ውድ አንባቢ ሆይ ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋራ ከተባበርን ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ እርሱን እንመሰለዋለን ሞት የማይቀር እዳ ሆኖ ብንሞትም መነሳታችን ግን አይቀርም በመሬት ላይ የተዘራ የስንዴ ቅንጣት መጀመሪያ ይበሰ...

የፍቅርህ እሳት /ጸሎት/

                 የፍቅርህ እሳት     ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ »   የፍቅርህ እሳት ይነድዳል በየዘመናቱም አዲስ ነውና ሙቀት ያላገኙትን በሃጢአት ቅዝቃዜ በቂምና በበቀል ብርድ የሚንዘፈዘፉትን ነፍሳት በህያው ሙቀቱ ከልብና ከህሊና ሞት ይታደጋል ።     መድሃኒቴ ሆይ » ፍቅር የሚለውን ታላቅ እውነት የተማርኩት ካንተው ነው ። ጥርስ ያወለቀ ጥርሱ እንዲወልቅ አይን ያጠፋ አይኑ እንዲጠፋ በታወጀበት አለም ምህረትና ይቅርታ መውደድና ማፍቀር ሰማእትነት እና ፍጹምነት ከባህሪህ አውጥተህ ስላሳየከኝ ባንተ የነበረው አሳብ በእኔም እንዲኖር ስላበረታከኝ ሁሉን ባንተ ስለተማርኩኝ መውደድን መወደድን ያየሁብህ ወዳጄ አመሰግንሃለው ።     አለሙን አንድ ያደረግከው ሆይ» ላንተ መገዛቴ በሙሉ ሃይሌ እና ጉልበቴ ነው ። ደምህ የሃጢአቴን ብዛት ጠርጎ አስወግዶልኛል ቁስልህ የነፍሴን ቁስል ፈውሶልኛል  ጥምህ የነፍስ ጥሜን ቆርጦልኛል መራብህ የዘለአለም ርሃቤን አስወግዶልኛል የሆንክልኝ ሁሉ ከቃላት በላይ ነው ባወራም ብናገርም ማለቂያ የለውም ።      ሰላሜ ሆይ » የነበረህን ያንን ሁሉ ክብር ትተህ እንደ ምስኪን ደሃ ማደሪያ እንደሌለው መንገደኛ ተንከራትተህ በቤትህ ያሉትን ዘጠና ዘጠኙን ሰራዊትህን ትተህ  በአባትነት ፍለጋህ ያገኘከኝ የማርከኝ የመንግስትህ ዜጋ ያደረከኝ አንተ ለእኔ የዘለአለም መኖሪያዬ ነህ መጠጊያዬና አምባዬ ነህ ።      ውዴ» እንደምወድህ አንተው ታውቃለህ ለእኔ ደስታ እንደደከምክ በድካም እንዳስደስትህ እተጋለሁ የከ...

ኒቆዲሞስ

Image
                       ኒቆዲሞስ 

ኒቆዲሞስ

                         መክሊት               የጽሁፌ መነሻ ማቴ 25፥14-23   ነው ። መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  በምሳሌ  ስለ መንግስተ ሰማያት  ካስተማረው ትምህርት በጠቀስነው ጥቅስ ውስጥ ተደጋግሞ የተነገረውን ቃል በምሳሌነት ይዘናል  <መክሊት >  አፌን በምሳሌ እከፍታለው  መዝ   77 እንዳለው መዝሙረኛው ጌታችንም ለሚከተሉት ሁሉ  ለነጋዴው በንግዱ ስርአትና በገንዘብ ፣ለገበሬው በእርሻና በዘር ፣ ለቤት እመቤቶች /ለሴቶች / በቡኮና በእርሾ እየመሰለያስተምር ነበር  ።        የባሮቹ ጌታ ወይም ንጉስ ወደሩቅ ሃገር ሊሄድ ሲል ባሮቹን ጠርቶ ለአንዱ አምስት መክሊት ፣ለሁለተኛው ሁለት መክሊት ፣ለሶስተኛው  አንድ መክሊት ሰጣቸውና እስክመጣድረስ ሰርታችሁ አትርፋችሁ ጠብቁኝ ብሎ ጥብቅ አደራ ሰጥቶአቸው  ሄደ ይላል ታሪካዊው ምሳሌ ።   ውድ የእግዚአብሄር  ልጆች ንጉሳችን ክርስቶስ በስጋ ማርያም ተገልጦ በምድር ላይ ማድራዊ ብቻ ሆነን እንድንቀር ያደረገንን በደም በውርስ ከእርግማን በታች ያደረገንን ዘለአለማዊ ሞት በሞቱ ደምስሶልን አዲስ የህይወት ምእራፍ ከፍቶልናል ። ታዲያ ይህንን ለሁላችን የሚሆን የመዳን ጸጋ ያለ አድልዎ ባጎናጸፈን ጊዜ የክርስትናን የእውነተኛውን  ሃ...

ጠላቱን አግኝቶ በመልካም መንግድ የሚሸኝ ማን ነው? by Kesis Tizitaw Samuel /video/

Image
LIQE MEZEMIRAN KESIS TIZITAW SAMUEL.

አስገራሚው የፍቅር ታሪክ

                    አስገራሚው የፍቅር ታሪክ         በመጀመሪያ እግዚአብሄር ሰማይና ምድርን ፈጠረ ስማይና ምድር ሲፈጠሩ አሁን በሰማይና በምድር ውስጥ ያሉት ፍጥረታት በሙሉ በእግዚአብሄር ቃል ሆኑ ፍጥረትን ሁሉ አስቦ በቃሉ የፈጠረው አምላክ በራሱ አርአያ እና አምሳል አዳምን ከአፈር አበጀው የህይወት እስትንፋስን በአፍንጫው እፍ አለበት ህያውም ሆነ የህይወት መመርያ ተሰጠው የተሰጠውን ነጻነት ተጠቅሞ የቀረበለትን ምርጫ ከህይወት አጋሩ ከሄዋን ጋር ተስማምቶ ሞትን መረጠ  የእግዚአብሄርም ቅን ፍርድ በላዩ ወደቀበት ስለዚህ ልጅነቱን ጸጋውን ክብሩን ስልጣኑን ተቀማ  ።         ይህ ታሪካዊ ስህተት የሰው ልጆችን ነጻነት ጠቅልሎ አስሮ በመቃብር የቀበረ የአለማችንን መልክ  የህይወታችንን ውበት በሞት ጥላሸት ለቅልቆ ያበላሸ በመጀመሪያው ንጹህ ታሪካችን ላይ ጠባሳ የጣለ ክስተት ነበር ። በሄዋን ማህጸን በአዳም አብራክ ውስጥ ሆነን ሁላችንም ተረገምን፣የሞትን ፍርድ ተቀበልን ። ቅ/ጳውሎስ ይህንን ሲያብራራ < ስለዚህ ምክንያትሃጢአት  በአንድ ሰው ወደ አለም ገባ በሃጢአትም ሞት እንደዚሁም ሁሉ ሃጢአትን ስለደረጉ ሞት  ለሰው ሁሉ ደረሰ ።> ሮሜ 5፥12 ይህ መጽሃፍ ቅዱሳዊ ቃል እንደሚያስረዳን በዘር እየተላለፈ ትውልድን ሲጨርስ የነበረው ሞት መንስኤው የአዳም በደል እንደሆነ በተጨማሪም ቀጥሎ የተፈጠረው ትውልድም በሃጢአት ባህር ውስጥ የተነከረ ማንነት...

<<< የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም >>>

                 <<<  የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም >>>           ከዚህ በፊት በዚሁ የእግዚአብሄር አሳብ ላይ ባሰፈርኩት ጽሁፍ የተወሰኑ ጉዳዮችን ተመልክተናል ዛሬ ተከታዩን ክፍል እናያለን ። ሶስት መቶ ቀበሮዎችን ሶምሶን ይዞ በጅራታቸው ላይ ችቦ አሰረባቸው እሳት ለኩሶ በጠላት አውድማ ላይ ለቀቃቸው የታሰረባቸውን እሳት ይዘው ሮጡ ተልእኮዋቸውንም ፈጸሙ ። መሳፍንት 15፥4 ሶስት መቶ ሰራዊት ለእልፍ አእላፍ ጠላት ይበቃል ይህ የሚሆነው ግን ተልእኮው እግዚአብሄር ያለበት ሲሆን ነው ። በመሰረቱ እግዚአብሄር በቁጥር ብዛት አያምንም በሶስት መቶ የጌዴዎን ሰራዊት እንደ አንበጣ እስራኤልን የወረረውን መንጋ እንዳልነበረ አድርጎታል መሳፍንት 7፥1-25 ። ወደ አዲስ ኪዳን እውነትም ስንመጣ ህይወታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለወንጌል አገልግሎት የመረጠው 12ቱን ሃዋርያት ነበረ ከእነርሱም ጋር የተደመሩት 120 የወንጌል እና የአዲስ ኪዳን ቤተሰብ ብቻ ነበሩ ። ዛሬ አለምን የከደነው ወንጌል በነዚህ ጥቂት ሰዎች አገልግሎት  ተጀምሮ ነው ለሁላችን የተረፈው ። በጥቂቶች ብዙ መስራት ለሚችል የሃይሉ እና የጥበቡ ብዛት ለማይለካ ለእግዚአብሄር ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ክብር ይሁን አሜን ።                   የዛሬዋም የከርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ኢያሱስ የጣለባትን የወንጌል አደራ በአግባቡ እንዳትወጣ የወንጌሉንም አላማ የጨበጡ  አገልጋዮች ለመንገዱ በተፈቀደው ፍጥነት ሮጠው ወንጌልን እንዳ...