እንዴት እንጹም ?
እንዴት እንጹም ? ጾማችን የሚጠበቅበትን ውጤትማምጣት እንዲችል የሚከተሉት የቅድስና ተግባራት አብረውት ሊከናወኑ ይገባል ፤ 1/ ከንቱ ውዳሴ የሌለበት ሊሆን ይገባል ፦ ጌታችን በወንጌል ማቴ 6፥16 ስትጦሙም እንደ ግብዞች አትጠውልጉ ለሰዎች እንደu ጡዋሚ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና እውነት እውነት እላቹሃለው ዋጋቸውን ተቀብለዋል ። ይህ ማለት ዋጋ ከሰማይ የማያመጣ ከንቱ የሆነ ድካም ነው ።ስለዚህ የጾማችን አላማ የሰዎችን ትኩርት መሳብሳይሆን የአምላካችንን ምህረት መውረስ ሊሆን ይገባል። 2/በፍቅርና በአንድነት፦ የቤተ ክርስቲያናችን የዜማ ሰው ቅ/ያሬድ <ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ ወንትፋቀር በበይናቲነ> ማለት- ጾምን እንጹም ወንድማችንን እንውደድ እርስ በእርሳችንም እንዋደድ።በማለት ጾም ከፍቅር ጋር ወንድምን ከመውደጋር ሊሆን እንደሚገባ ይናገራል።የተወደዳችሁ ክርስቲያኖች ያለ ፍቅር የቱንም ያህል በእያንዳንዱ አገልግሎት ብንሰማራ ...