እንዴት እንጹም ?

                            እንዴት እንጹም ?

ጾማችን የሚጠበቅበትን ውጤትማምጣት እንዲችል የሚከተሉት የቅድስና ተግባራት አብረውት ሊከናወኑ ይገባል ፤

1/ ከንቱ ውዳሴ የሌለበት ሊሆን ይገባል ፦ ጌታችን በወንጌል ማቴ 6፥16 ስትጦሙም እንደ ግብዞች አትጠውልጉ ለሰዎች
    እንደu ጡዋሚ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና እውነት እውነት እላቹሃለው ዋጋቸውን ተቀብለዋል ። ይህ ማለት ዋጋ ከሰማይ
    የማያመጣ ከንቱ የሆነ  ድካም ነው ።ስለዚህ የጾማችን አላማ የሰዎችን ትኩርት መሳብሳይሆን የአምላካችንን ምህረት መውረስ
    ሊሆን ይገባል።

2/በፍቅርና በአንድነት፦ የቤተ ክርስቲያናችን የዜማ ሰው ቅ/ያሬድ <ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ ወንትፋቀር በበይናቲነ> ማለት-
   ጾምን እንጹም ወንድማችንን እንውደድ እርስ በእርሳችንም እንዋደድ።በማለት ጾም ከፍቅር ጋር ወንድምን ከመውደጋር ሊሆን         እንደሚገባ ይናገራል።የተወደዳችሁ ክርስቲያኖች ያለ ፍቅር የቱንም ያህል በእያንዳንዱ አገልግሎት ብንሰማራ                          ውጤቱ በዜሮ ይባዛል ።

3/ከምጽዋት ጋር ፦ አንዳንድ ሰዎች በጾማቸው ወቅት ቁርሳቸውን አንዳንዶቹም ምሳቸውን ስለማይመገቡ ያንኑ ገንዘብ ያጠራቅሙትና ቅድስና ለማያተርፍ ለሌላ አገልግሎት ማለትም ስጋዊ ጉድለታቸውን ለመሸፈን ይጠቀሙበታል ። ይህ ክፉ
ነገር ሆኖ ሳይሆን ለምጽዋት እጃችንን እንዳንዘርጋ ስለሚያስረን ነው ። ጾም ያለ ምጽዋት ያልሟላ ውበት ማለት ነው።
የማቴዎስ ወንጌል ም6 ሙሉውን ስናነብብ ተቆራኝተው የሚሄዱ የክርስትና መርሆዎችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዝርዝር
አስቀምጦአቸው እናገኛለን እነርሱም ምጽዋት-ጸሎት-ጾም  እነዚህ በፍጹም የማይለያዩ ነገሮች ናቸው ። ይህንን ጌታ ሲያብራራው
<በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ ።ለድሆችና የሚበሉት የሚለብሱት ለሌላቸው ከሙላትም ከጉድለትም ላይ ማካፈል ማለት  ብልና ዝገት በማያጠፉት ሌባ በማይዘርፈው በሰማይ ካዝና ውስጥ የተጣራ ትርፍ< net profit > ማስቀመጥ ማለት ነው ።
  ይቀጥላል   ቀሲስ ትዝታው ሳሙኤል

Popular posts from this blog

አስገራሚው የፍቅር ታሪክ