እንዴት እንጹም ከባለፈው የቀጠለ፥
እንዴት እንጹም ከባለፈው የቀጠለ፥
ጾም እና ጸሎት በንግግር ውበት ብቻ ሳይሆን በአንድምታም ፤ በክርስትና መርህም የማይነጣጠሉ የአምልኮ ስርአቶች ናቸው ። በመሰረቱ ጾማችን መጾም ስላለብን እና በአዋጅ ሁሉም ስለ ጾመ በልምድ መሆን የለበትም
በዓላማ በአጀንዳ ማለትም በጾሙ መጨረሻ ከጌታ ደጋግ መዳፎች አንድ የምንቀበለው ነገር እንዲኖር በቆረጠ
መንፈስ በዝግጅት ልንጾም ይገባል ። ውጤት የሌለው ነገር ሲደጋገም ተስፋ ያስቆርጣል ስለዚህ ጾሙ ዞሮ ሲመጣ
የመጾም ሃይላችንን ያሳንሰዋል ሞራላችንን ይጎዳዋል ስለዚህ በጉዳይ የመጾም አቅም ለራሳችን እናሳድግ ።
እግዚአብሄር የልባችንን ጥያቄ ይመልስልን።
ያለ እምነት ሊከናወን አይችልም ። የምንጾመው በእምነት ሊሆን ይገባል ፦ ሀ/ ጾም የእግዚአብሄር መለኮታዊ አሳብ እንደሆነ ለ/ በጾም እግዚአብሄር ሃገርን ይቅር እንደሚል ሐ/ ከጾማችን ጋራ የምናቀርበው ልመና እንደሚመለስልን
መ/ ከልባችን በቅድስና በምንጾመው ጾም ነፍሳችንን በጾም ለእርሱ በማስገዛታችን በደስታ እንደሚቀበለው
ይህንን በማመን ልንጾም ይገባል ።
በመጨረሻም፦ በቂም፣ በበቀል፣ ሰራተኞቻችንን በመበደል፣ በመዋሸት፣ የስጋ ፈቃዳችንን በመፈጸም፣ክፉ በመናገር፣ሰዎችን በመክሰስ ፣በጥል፣በክርክር፣ ያለ ንሰሃ የምንጾመው ጾም በአምላካችን ፊት ተቀባይነት የለውም ። ራሱ አምላካችን እግዚአብሄር <እኔ የመረጥኩት ጾም ይህ ነውን?>በማለት ይጠይቃል ኢሳያስ 58፥3-14
በዚህ ርኩሰት ውስጥ ሆነን ብንጾም ከንቱ ርሃብ ወይም የርሃብ አድማ ከመሆን ውጪ ሰማይዊ በረከት እና ምላሽ
የማይሰጥ እንደሆነ የተጠቀሰውን ምእራፍ ሙሉውን ስናነብብ እናረጋግጣለን ።
ጾማችንን የድል የበረከት ያድርግልን ። አሜን ።
4/ከጸሎት ጋር ፥
ውድ አንባብያን በዚህ የእኛ ልዩ እድል በሆነው የጌታችን ጾም ውስጥ እያንዳንዳችን ከሰማይ መልስ የሚጠብቁ የግል ጥያቄዎች አሉን እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ላንሳ ስንቶቻችን ሃይምኖታዊ {ክርስቲያናዊ} እና ሃገራዊ ጥያቄዎች ይዘን በጌታ ፊት ቆመናል የክርስቶስ ፍቅር ልቡን ያሳረፈለት የተደላደለ መንፈሳዊ አቛም ያለው ሰው
ከግል ጥያቄው እኩል ስለ ሃይማኖቱ ሰላም ስለ ወንድሞቹ እና እህቶቹ የህይወት ስኬት ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት አልፎ ተርፎ ስለ ዓለም ሁሉ ይጸልያል ። ክርስትና ሲያድግ ልብ ይሰፋል በሰፊ ልቡ ደግሞ መታሰብ ያለባቸው ጠቅላላ ጉዳዮችን በጾሙም በጸሎቱም ክበቡን ሳያጠብብ ሁሉን ያስባል ። ከዚህ እውነት በመነሳት የራሳችንን ህይወት እንድንዳስስ አሳስባለሁ ።ጾም እና ጸሎት በንግግር ውበት ብቻ ሳይሆን በአንድምታም ፤ በክርስትና መርህም የማይነጣጠሉ የአምልኮ ስርአቶች ናቸው ። በመሰረቱ ጾማችን መጾም ስላለብን እና በአዋጅ ሁሉም ስለ ጾመ በልምድ መሆን የለበትም
በዓላማ በአጀንዳ ማለትም በጾሙ መጨረሻ ከጌታ ደጋግ መዳፎች አንድ የምንቀበለው ነገር እንዲኖር በቆረጠ
መንፈስ በዝግጅት ልንጾም ይገባል ። ውጤት የሌለው ነገር ሲደጋገም ተስፋ ያስቆርጣል ስለዚህ ጾሙ ዞሮ ሲመጣ
የመጾም ሃይላችንን ያሳንሰዋል ሞራላችንን ይጎዳዋል ስለዚህ በጉዳይ የመጾም አቅም ለራሳችን እናሳድግ ።
እግዚአብሄር የልባችንን ጥያቄ ይመልስልን።
5/በእምነት እንጹም ፦
ውድ ክርስቲያኖች ያለ እምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻልም ብሎ መጽሃፍ እንደተናገረ ጾማችንምያለ እምነት ሊከናወን አይችልም ። የምንጾመው በእምነት ሊሆን ይገባል ፦ ሀ/ ጾም የእግዚአብሄር መለኮታዊ አሳብ እንደሆነ ለ/ በጾም እግዚአብሄር ሃገርን ይቅር እንደሚል ሐ/ ከጾማችን ጋራ የምናቀርበው ልመና እንደሚመለስልን