Posts

እውነት ኢየሱስ ነው።

                          እውነት 2/ኢየሱስ የዘለዓለም እውነት ነው            እውነትን የሚተካው ብቸኛው ትርጉም በስጋ የተገለጠው አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። ጲላጦስ አይሁድ ክርስቶስን አሳልፈው በሰጡት ምሽት የዓለማችንን ትልቅ ጥያቄ ለጌታ አቀረበለት <እውነት ምንድነው?>ዮሐ 18፥38 ይህ ጥያቄ ዛሬም ክርስቶስን ለማያውቁ እና ለማያምኑ ሁሉ በደማቁ ተጽፎ ህሊናቸውን የሚሞግት ብርቱ ጥያቄ ነው ። ለእኛ ለምናምነው እና ለምንከተለው ወገኖቹ ግን የዘለአለም ጥያቄያችንን የመለሰው የዘላለም መልሳችን እና እውነታችን ኢየሱስ  ነው ።          ወገኖቼ ዛሬ የጥያቄያችን መልስ አለማግኘት ብቻ ሳይሆን የሚያሳስበን ያገኘነው መልስ የቱን ያህል እውነተኛ ነው የሚለው ነው የሚያስጨንቀን ። ስለ እውነት ጠይቀን ሃሰት የተነገረን ስለእውነት ተከራክረን በሃሰት ቃል የተረታን በህዝብና በአህዛብ ፊት የተገለጠውን ሃቅ በተቀነባበረ ምስልና ድምጽ ብሎም የቃላት ውርጅብኝ ውሸት ነው የተባልን በአጠቃላይ እውነትን የተቀማን ሁሉ እውነታችን የናዝሬቱ ኢየሱስ ነው ።           ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም ዘሁል 23÷19 ይላል መፅሐፍ ማለትም ሰው ሃሰተኛ ጌታ እውነተኛ ነው ።አንዳንድ ሰዎች ከሃሰት ከክህደት ውጪ ስራ የሌላቸው ናቸው ይህንን ክፉ በሽታ ደግሞ እንደ ህይወት መመሪያ አድርገው ይኩራሩበታል "ካልዋሸህ አትኖርም" የሚለውን  የሰነፎች ተረት አታሞ እየመቱ ያዜሙታል...

Kesis Tizitaw Samuel New Mezmur YEMESKELU SERAWIT

Image
LIQE MEZEMIRAN KESIS TIZITAW SAMUEL.
https://youtu.be/3C7c5qpV000 YEMESKELU SERAWIT NEW SINGLE MEZMUR  BY LIQE MEZEMIRAN KESIS TIZITAW SAMUEL

አስተርእዮ

                        አስተርእዮ      «የዲያብሎስን ስራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ለጅ ተገለጠ»1ኛ ዮሐ3፥8 አስተርእዮ ማለት በአጭር ቃል መገለጥ ማለት ነው ። የማይታየው አምላክ(የመለኮት ባህሪ የስጋን ባህሪ ገንዘቡ አድርጎ በተዋህዶ ሲያከብረን) ሥጋ ለብሶ ታየ ተገለጠ፣የማይራበው ተራበ፣የማይጠማው ተጠማ፣ የማይዳሰሰው ተዳሰሰ፣የማይረታው ተረታ፣የማይደፈረው ተደፈረ ፣የማይሞተው ሞተ በዚህም ሁሉ ድንቅ ስራ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ ያለው ልዩ ፍቅር ተገለጠ ታየ ታወቀ <አስተርእዮ>።        በዮርዳኖስ ወንዝ ዳር ጌታ በሎሌው እጅ ከተጠመቀ በኋላ ከውሃው ሲወጣ መንፈስ ቅዱሰ  በርግብ አምሳል ከማደሪያው መጥቶ በኢየሱሰ  አናት ላይ አረፈ አብ ደግሞ በነጎድጓድ ድምፁ እያስተጋባ እያንጎደጎደ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት ሲል ተደመጠ ፣የአብ አባትነት ፣የወልድ ልጅነት፣ የመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት በልዩ ግርማና ክብር ተገለጠ የፈቃድ አንድነት እና የአካል ሶስትነት ተገለጠ።ማቴዎስ 3፥1-ፍጻሜ።        ክርስትና የተገለጠ የመገለጥ ሃይማኖት ነው ። የምናምነው በተገለጠው ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው ያዳነንም በህዝብና በአህዛብ ፊት በተገለጠው ፍቅሩ ነው ።ዮሐንስ በወንጌሉ «እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው »ዮሐ 1፥18 በተደጋጋሚ አባቴ እያለ ስለ አባቱ አጽናኙ እያለ መንፈስ ቅዱስን የተረከልን የሰማዩን ምስጢር ያስተማረን የተረከልን ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። ለአምል...

እወዳለሁ ንጻ ሉቃስ5፥12

                       <<እወዳለሁ ንጻ>>                           የሉቃስ ወንጌል 5፥12-16         ውድ የእግዚአብሔር ልጆች እንደምን ሰነበታችሁ የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ ።በዛሬው የወንጌል ጦማር የምናነበው የጌታችንን መለኮታዊ ተአምር  ሲሆን ተከትሎም ለሁላችን ስለተደረገልን ታላቅ ውለታ እናጤናለን ፣      ክርስቶስ በምድር ላይ በስጋ የተገለጸው ለሁለት ታላላቅ  ምክንያቶች ነው ።  1/ሁላችንን ለማዳን     2/ለዘላለም አርአያነት  በስጋ በተገለጠበት የስጋዌው ወራት ህሙማነ ነፍስን {ነፍሳቸው የታመመባቸውን }በትምህርቱ  ህሙማነ ስጋን በተአምራቱ በአምላካዊ ሃይሉ እየፈወሰ መድሃኒት ሆኖ መገለጡን በሚያስመሰክር ታላቅነት ለምጻሞችን ሲያነጻ፣ ጎባጣውን ሲያቀና፣እውራንን ሲያበራ፣ሽባዎችን ሲተረትር ፣ ልምሾዎችን ሲያጸና ፣ ሃጢአተኛ ተብለው የተፈረደባቸውን በሰላም ሂድ በሰላም ሂጂ እያለ ሲያሰናብት ፣በአጋንንት ክፉ እስራት ውስጥ ወድቀው የሚማቅቁትን የመቃብር ዳር ምስኪኖች ከስቃይ ሲገላግል ,,,,,,,,,ወዘተ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት በመጽሃፍ ቅዱስ ምስክርነት እናረጋግጣለን ።         በፍቅሩ የፍቅር ትርጉም የሆነው ጌታ የእውቀት አስተማሪ ጥበብ አሳማሪ ህግ ሰሪ መሆኑን ለመግለጽ ብዙ ጊዜ አልወሰደም ...

ሕይወት ኢየሱስ ነው ።

                     ሕይወት ኢየሱስ ነው ።                 <<ሕይወት ተገለጠ አይተንማል >>1ኛ ዮሐ 1፥2 በሞት ተሸንፎ ለወደቀው አለም የተገለጠው ሕይወት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። ኢየሱስ ሕይወት ብቻ ሳይሆን የዘለአለም ሕይወት ነው ። 1ኛ ዮሐ 5፥20 በጥንታዊው ሰው በአዳምና በአጋሩ በሔዋን አለመታዘዝ ምክንያት ሕይወት የውሃ ሽታ ሆኖ የገነት ደጃፎች ተከርችመው የሲኦል መግቢያ ወለል ብሎ ተከፍቶ ከአቤል ግድያ እስከ ክርስቶስ መስዋእትነት ድረስ እጅግ ብዙ ነፍሳትን ውጧል ሞት በሃጢአት ምክንያት የመጣብን የበደላችን ዋጋ ስለሆነ ከህይወት ተለይተን ኖረናል ።        የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ እንዳለው 1ኛ ዮሐ 3፥8 ጌታችን የመጣው በዲያብሎስ ተንኮል የተተበተበውን የሞት መረብ በጣጥሶ ነጻነት ሊሰጠን ነው ። ስለዚህ ህይወት ሲገለጥ ሞት መግቢያ መውጫ ጠፋው በመስቀል ላይ በደም ታነቀ፣ ታሰረ፣ኢየሱስ ጠላታችንን በመስቀሉ ጠርቆ አስሮ ነፍሱን ከስጋው በገዛ ስልጣኑ ለይቶ በአካለ ነፍስ በግርማ ወደ ሲኦል ወርዶ ለዘመናት በባርነት የተገዛውን አዳምን ከልጅ ልጆቹ ጋር ነጻ አወጣው ። ሲኦል ባዶ ቀረ ክርስቶስ ከበረ። ያን ጊዜ የዘለአለም ሕይወት ለሰዎች ሁሉ ተመልሶ ተሰጠን ። ውድ ክርስቲያኖች ይህ ውድ ዋጋ የህይወት መሷእትነት የተከፈለው ለእኔም ለአንተም ለአንቺም መሆኑን አምነን ለክርስቶስ ፍቅር ልንገዛ ልናመልከው ልናመሰግነው ይገባል ። ዮሐ 3፥16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ...

መንገድ እውነት ሕይወት ዮሐ 14፥6

                    መንገድ እውነት ሕይወት                                               ዮሐንስ 14÷6         ውድ   የዚህ መንፈሳዊ ድህረ ገፅ አንባቢዎች እንደምን ከርማችኋል የጌታ ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ  በዚህ ፅሁፍ ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን ሶስት ታላላቅ ቃላቶች በተራ ትርጉማቸውን እያየን የመድሃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን  ታላቅ የማዳን ስራ እንመሰክራለን ።      የዚህ አለም የኢኮኖሚ ተንታኞች ለአንዲት አገር ፈጣን እድገት እና ልማት ትልቁን ድርሻ የሚወስደው መንገድ እንደሆነ ይስማማሉ ። በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ክፍላተ ሃገራትን እንዲሁም ከአዋሳኝ አገራት ጋር የንግድ የባሕል የኢኮኖሚ ልውውጦችን ለማድረግ ጉልህ ድርሻ የሚወጣው መንገድ እንደሆነ ያረጋግጣሉ ሃሳቡ ከእውነት ያልራቀ ስለሆነ እኛንም ያሳምነናል ። በሃይማኖታዊ እይታም መሰረት መንገድ ብዙ ሚስጥራትን የያዘ ቃል ነው ስለዚህ የዚህ ዓለም ጠበብቶች የተስማሙበትን የመንገድን አስፈላጊነት ማለትም በድንጋይ ወይም ዘመናዊው አስፋልት አልያም የጥርጊያ መንገድ ሁሉም እንደየአቅማቸው ለህብረተሰቡ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ከግምት ውስጥ በማስገባት እኛ ልንለው የምንችለውን ፈርጥ እውነት ከፍ አድርገን እናሳያለን ።               ...