አስተርእዮ
አስተርእዮ
«የዲያብሎስን ስራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ለጅ ተገለጠ»1ኛ ዮሐ3፥8
አስተርእዮ ማለት በአጭር ቃል መገለጥ ማለት ነው ። የማይታየው አምላክ(የመለኮት ባህሪ የስጋን ባህሪ ገንዘቡ አድርጎ በተዋህዶ ሲያከብረን) ሥጋ ለብሶ ታየ ተገለጠ፣የማይራበው ተራበ፣የማይጠማው ተጠማ፣ የማይዳሰሰው ተዳሰሰ፣የማይረታው ተረታ፣የማይደፈረው ተደፈረ ፣የማይሞተው ሞተ በዚህም ሁሉ ድንቅ ስራ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ ያለው ልዩ ፍቅር ተገለጠ ታየ ታወቀ <አስተርእዮ>።
በዮርዳኖስ ወንዝ ዳር ጌታ በሎሌው እጅ ከተጠመቀ በኋላ ከውሃው ሲወጣ መንፈስ ቅዱሰ በርግብ አምሳል ከማደሪያው መጥቶ በኢየሱሰ አናት ላይ አረፈ አብ ደግሞ በነጎድጓድ ድምፁ እያስተጋባ እያንጎደጎደ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት ሲል ተደመጠ ፣የአብ አባትነት ፣የወልድ ልጅነት፣
የመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት በልዩ ግርማና ክብር ተገለጠ የፈቃድ አንድነት እና የአካል ሶስትነት ተገለጠ።ማቴዎስ 3፥1-ፍጻሜ።
ክርስትና የተገለጠ የመገለጥ ሃይማኖት ነው ። የምናምነው በተገለጠው ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው ያዳነንም በህዝብና በአህዛብ ፊት በተገለጠው ፍቅሩ ነው ።ዮሐንስ በወንጌሉ «እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው »ዮሐ 1፥18 በተደጋጋሚ አባቴ እያለ ስለ አባቱ አጽናኙ እያለ መንፈስ ቅዱስን የተረከልን የሰማዩን ምስጢር ያስተማረን የተረከልን ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። ለአምልኮአችን እንግዳ አይደለንም የምናመልከውን አምላክ ተገልጦ አይተነዋል ።
ክርስትና በእውነት ምስክርነት ላይ የቆመ እምነት ነው ፤ ባለንስር አይኑ ሃዋርያ ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሃንስ ወንጌላዊ በመልእክቱ ይህንን እውነት ያረጋግጥልናል « ስለ ህይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውን እና የሰማነውን በአይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘለአለምን ሕይወት እናወራላችኋለን »1ኛ ዮሐ 1፥1።ይህ ምስክርነት የሁላችንን ልብ የደገፈ ያሳረፈ ነው እርግጠኞች ሆነን ሰማይን ተስፋ የምናደርገው በተገለጠው የዘለአለም ሕይወት በኢየሱስ ክርስቶስ ነው ።
«የእርሱን ግርማ አይተን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መምጣት አስታወቅናችሁ,,,,,»2ኛ ጴጥ 1፥16-19 በደብረታቦር ተራራ ላይ የተገለጠውን ግርማ መለኮት ከሰማይ የመጣውን የአባቱን የምስክርነት ድምጽ አይተው ሰምተው አረጋግጠው ለዚህ እውነት ምስክሮች እንደሆኑ ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ አድርጎ ጽፎልናል ።
በዚህ ታላቅ መገለጥ ውስጥ እኛም በክብር ተገልጠናል ለረገጠን ጠላታችን ፣ ለገደለን ሞታችን ለመቃብራችን፣ ለሲኦል፣ ለዓለም አሸናፊ አድርጎ ገልጦናል መቃብራችንን ረግጠን« ሞት ሆይ መውጊያህ የታለ ሲዖል ሆይ ድል መንሳትህ ወዴት አለ » ብለን የምንዘምር ባለቅኔዎች አድርጎናል ።
ውድ ክርስቲያኖች ክርስትና ስም ብቻ ሳይሆን ሕይወት ነው ይህ የዛሬው በመገለጥ ላይ የተመሰረተው አጭር ክታቤ መጠቅለያ ከዚህ የሚከተለው ይሆናል ። ከክርስቶስ ስሙን ብቻ ሳይሆን ሕይወቱን፣ብርሃኑን፣ሰላሙን፣ፍቅሩን፣ ታሪኩን ብቻ ሳይሆን ተግባሩን ,,,, በአጠቃላይ ማንነቱን አጋርቶናል የዘረዘርናቸውና ያልዘረዘርናቸው የጌታችን ባህሪያት በሙሉ በጸጋ የተቀበልናቸው እና ለሌሎች እንድናካፍላቸው የተሰጡን የፍቅር ስጦታዎች ናቸው መክሊታችን ለትርፋችን የተሰጠን ታላቅ አደራ ነው ከጎኑ የፈሰሰው ደሙ በእጆቹና በእግሮቹ የተሰነቀረው ችንካሩ በእራሱ ላይ የተተከለው የእሾህ አክሊል በአይሁድ ጅራፍ የታረሰ መሬት የመሰለው ጀርባው,,,,ወዘተ ሁሉም ለኛ የተከፈለ የፍቅር ዋጋ ነው ። ከጌታ የተቀበልነውን ብርሃን ለሌሎች ልናበራበት ፣ በፍቅሩ ሌሎችን ልንወድበት ፣በይቅርታው ሌሎችን ይቅር ልንልበት ይገባል «ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ሁሉ ፊት ይብራ»ማቴ5፥16 እንዳለው ጌታ ለዚህ ጨለማ ዓለም ከጌታ የተቀበልነውን ብርሃን ልናበራለት ይገባል በተገለጠ ክርስትና ውስጥ ሆኖ የራስን ክርስትና አለመግለጥ ሽንፈት ነው ።ተገልጦ ለዓለም የገለጠን ጌታ ዘለዓለም ይባረክ።አሜን።