ሕይወት ኢየሱስ ነው ።
ሕይወት ኢየሱስ ነው ።
<<ሕይወት ተገለጠ አይተንማል >>1ኛ ዮሐ 1፥2
በሞት ተሸንፎ ለወደቀው አለም የተገለጠው ሕይወት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ።
ኢየሱስ ሕይወት ብቻ ሳይሆን የዘለአለም ሕይወት ነው ። 1ኛ ዮሐ 5፥20 በጥንታዊው ሰው በአዳምና
በአጋሩ በሔዋን አለመታዘዝ ምክንያት ሕይወት የውሃ ሽታ ሆኖ የገነት ደጃፎች ተከርችመው የሲኦል
መግቢያ ወለል ብሎ ተከፍቶ ከአቤል ግድያ እስከ ክርስቶስ መስዋእትነት ድረስ እጅግ ብዙ ነፍሳትን
ውጧል ሞት በሃጢአት ምክንያት የመጣብን የበደላችን ዋጋ ስለሆነ ከህይወት ተለይተን ኖረናል ።
የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ እንዳለው 1ኛ ዮሐ 3፥8 ጌታችን የመጣው በዲያብሎስ ተንኮል የተተበተበውን የሞት መረብ በጣጥሶ ነጻነት ሊሰጠን ነው ። ስለዚህ
ህይወት ሲገለጥ ሞት መግቢያ መውጫ ጠፋው በመስቀል ላይ በደም ታነቀ፣ ታሰረ፣ኢየሱስ ጠላታችንን በመስቀሉ ጠርቆ አስሮ ነፍሱን ከስጋው በገዛ ስልጣኑ ለይቶ በአካለ ነፍስ በግርማ ወደ ሲኦል ወርዶ ለዘመናት በባርነት የተገዛውን አዳምን ከልጅ ልጆቹ ጋር ነጻ አወጣው ። ሲኦል ባዶ ቀረ ክርስቶስ ከበረ።
ያን ጊዜ የዘለአለም ሕይወት ለሰዎች ሁሉ ተመልሶ ተሰጠን ። ውድ ክርስቲያኖች ይህ ውድ ዋጋ የህይወት መሷእትነት የተከፈለው ለእኔም ለአንተም ለአንቺም መሆኑን አምነን ለክርስቶስ ፍቅር ልንገዛ
ልናመልከው ልናመሰግነው ይገባል ።
ዮሐ 3፥16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ A,ለሙን እንዲሁ ወዶአልና ።
ዮሐ 5፥24 ቃሌን የሚሰማ የላከጝን የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው ።
ዮሐ 6፥40 ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገጝ የአባቴ ፈቃድ ይህነው
ዮሐ 6፥54 ስጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ህይወት አለው
ዮሐ 10፥27 በጎቼ ድምጼን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉጝማል እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ ለዘላለምም አይጠፉም ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም ።
እነዚህ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅሶች በሙሉ ወደ አንድ ታላቅ እውነት ያደርሱናል እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ምትክ የሌለው የዘለአለም ሕይወታችን እንደሆነ እና የዘለአለም ድህነታችን የተረጋገጠው በእርሱ መምጣት እንደሆነ ያረጋግጥልናል ።
የዘላለም ሕይወት ማለት እግዚአብሄር ያዘጋጀልን በክርስቶስ መምጣት የወረስናት {የምንወርሳት }
ዮሐንስ በራእዩ ከሰማይ ስትወርድ ያያት አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ናት በዚህች ዘላለማዊ እና ሰማያዊ
አገራችን ስንኖር ሞት የለብንም ፍርሃት፣ጭንቀት ፣ጩኸት፣ስቃይ፣ህመም ፣ ሃዘን ,,,,ወዘተ አያገጙንም
እነዚህ ኪሳራዊች በሙሉ የአሮጌው እና የሚያልፈው የዚህ አለም ስርአቶች ናቸው ይህ ስርአት በዘለአለም ሕይወት ውስጥ የሉም ራእይ 21፣1-4 ።
በምድር ያለቀስን በመንግስተ ሰማይ እምባችን ከአይናችን ይታበሳል ነጫጭ ልብስ ከብርሃን አክሊል ጋራ እንለብሳለን የበጉን ዙፋን ከበን የማይምት የዘላለም ቅኔ እንቀኛለን የአውሬውን ምልክት አልቀበልም ብለው የኢየሱስ ምስክር ሆነው ድል ከነሱት እልፍ አእላፋት እና ከመላእክት ጋራ በምስጋና የምንኖርበት ልዩ አለም ነው ።
መንግስቱን የሰጠን ለዘላለም የመረጠን የሁላችን አምላክ የዘላለም ህይወታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ምስጋና ልሁንለት ።
ቀሲስ ትዝታው ሳሙኤል።