Posts

መንገድ እውነት ሕይወት ዮሐ 14፥6

                    መንገድ እውነት ሕይወት                                               ዮሐንስ 14÷6         ውድ   የዚህ መንፈሳዊ ድህረ ገፅ አንባቢዎች እንደምን ከርማችኋል የጌታ ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ  በዚህ ፅሁፍ ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን ሶስት ታላላቅ ቃላቶች በተራ ትርጉማቸውን እያየን የመድሃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን  ታላቅ የማዳን ስራ እንመሰክራለን ።      የዚህ አለም የኢኮኖሚ ተንታኞች ለአንዲት አገር ፈጣን እድገት እና ልማት ትልቁን ድርሻ የሚወስደው መንገድ እንደሆነ ይስማማሉ ። በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ክፍላተ ሃገራትን እንዲሁም ከአዋሳኝ አገራት ጋር የንግድ የባሕል የኢኮኖሚ ልውውጦችን ለማድረግ ጉልህ ድርሻ የሚወጣው መንገድ እንደሆነ ያረጋግጣሉ ሃሳቡ ከእውነት ያልራቀ ስለሆነ እኛንም ያሳምነናል ። በሃይማኖታዊ እይታም መሰረት መንገድ ብዙ ሚስጥራትን የያዘ ቃል ነው ስለዚህ የዚህ ዓለም ጠበብቶች የተስማሙበትን የመንገድን አስፈላጊነት ማለትም በድንጋይ ወይም ዘመናዊው አስፋልት አልያም የጥርጊያ መንገድ ሁሉም እንደየአቅማቸው ለህብረተሰቡ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ከግምት ውስጥ በማስገባት እኛ ልንለው የምንችለውን ፈርጥ እውነት ከፍ አድርገን እናሳያለን ።               ...

ቀሲስ ትዝታው ሣሙኤል ንሰሃ እና ቅዱስ ቁርባን - Neseha And kidus Kurban,Kesis tizitaw Samuel Sibket Video

Image
LIQE MEZEMIRAN KESIS TIZITAW SAMUEL.

በአለም ሳለዉ የአለም ብርሃን ነኝ /Yealem Birhan/ Kesis Tizitaw Samuel Sebket Video

Image
LIQE MEZEMIRAN KESIS TIZITAW SAMUEL.

ወንጌል /ግጥም/

                  ወንጌል ወንጌል የምስራች ሰማያዊ ዜና የልባችን ደስታ የነፍሳችን መና ወንጌል ወንጀል ገዳይ ወንጌል ብሩህ ፀሐይ ጨለማ ገላጭ ነው የብርሃን ፀዳል ወደ ሰማይ መውጫ የህይወት መሰላል ከኢየሱስ አንደበት የተቀዳ ውሃ ዘንቦ ማያባራ ደስታና ፍስሃ ዶፍ ሆኖ ያራሰ የነፍስን በረሃ የማይጠፋ ችቦ ምስጋና ተከቦ በሶምሶን ቀበሮ በሃዋርያት ጅራት የታሰረ መብራት የሃጥያት አውድማን የዲያብሎስን ክንድ የበላ ነበልባል ያቃጠለ ሰደድ የፍቅር አዋጅ ነው አዲስ ኪዳን መንገድ ብሉይን ያስረጀ የይቅርታ ሰነድ ትንቢትን ተርጉሞ ሚስጥሩን የፈታ የእውነት ሰገነት የፍጥረት ከፍታ ልደቱን ጥምቀቱን ስቅለት ትንሳኤውን የኢየሱስን እርገት ዳግመኛ ምፅአቱን ዘርዝሮ የነገረን ቸርነቱን ፍቅሩን የመፃህፍት ራስ የኛም ልደት ቦታ ወንጌል መስታወት ነው የአምላክ አንድምታ የነፍስ አቡጊዳ የህይወት ሃሌታ የአዲስ ህይወት እድል የአፍ መፍቻ ፊደል እልፍ ቃል ነው ወንጌል ።         ቀሲስ ትዝታው ሣሙኤል

ጸሎት

                                    ጸሎት         ጸሎት ማለት ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር ማለት ነው ። በጸሎት የምንፈልገውን ነገር ሁሉ ከጌታ ዘንድ መጠየቅ እና ማግኘት  እንችላለን ። ከጸሃይ በታች ያለው ህይወታችን ጉድለት የበዛበት ሙሉ ሆኖ የማያውቅ ሙሉ መሆን የማይችል ቀዳዳ ነው ። በመሰረቱ ህይወት ጎዶሎ የሚሆነው ከምኞታችን አንጻር እንጂ ያለኝ ይበቃኛል ለሚል ሰው ጉድለቱን ሳይሆን ሁል ጊዜ የሚያየው  ሙላቱን ነው ስለዚህ በምስጋና የተሞላ ማንነት አለው ። በመሰረቱ አብዝቶ ከሚጸልይ ይልቅ አብዝቶ የሚያመሰግን ሰው ብዙ  በረከት ይቀበላል , መጽሃፍ ቅዱስ እንዳርጋገጠልን ጌታም እንዳስተማረው በቅድሚያ መንግስቱንና ጽድቁን ፈልጉ ሌላው ሁሉ  ይጨመርላችሃል ማቴ 6፥33 እንዳለው እኛ ለቃሉ በተገዛ ማንነት የዘላለም መኖሪያ የሆነችውን ርስታችንን መንግስተ ሰማያትን  ለመውረስ ጽድቅ በተባለው እውነት በኢየሱስ ክርስቶስ ለመዳን ብቻ ነው በጽኑ ማሰብ እና መፈለግ ያለብን ።      በዚህ የጸሎት አቅጣጫ እስከዛሬ የዘለቅንበትን የጸሎት ህይወት ለመገምገም እንሞክራለን , በጉድለት የተሞላውን ማንነታችንን በቃኝ የማያውቀው ፍላጎታችንን እንዲሁም ልጛም የሌለው የምኞት ፈረሳችንን ከአንድ ምእራፍ ለማሳረፍ ትልቁ መፍትሄ ጸሎት ነው ። በጸሎት ፈጣሪን ተማጽነው ጠላታቸውን የረቱ ፣ ከመካንነት ነቀፋ ተገላግለው በልጅ የተባረኩ ፣ ከሰው ያሳነሳቸውን አንገታቸውን ያስደፋቸውን መብላት እየፈለጉ እንዳይበሉ...

ትንሳኤ

        " ተነስቷል "    የተናገረውን የሚያደርግ የማያደርገውን የማይናገር በቃልም በግብርም የታመነው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀድሞ በገነት የሳተውን አዳምን እና በአዳም ውድቀት የወደቅነውን እኛ ሁላችንን ያጣናትን ሰማያዊት አገራችንን ሊመልስልን ከገባንበት ጨለማና ፍርድ ሊቤዠን የተናገራትን ቀን ቆጥሮ ተገለጠልን ።  በነገራችን ላይ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣው ለመሞት ነው ። ደም ሳይፈስስ ሰርየት የለም እንዳለው መጽሃፍ የእንስሳት እና የሰዎች ደም በክርስቶስ የመጣውን ስር ነቀል ለውጥ ሊያመጣ ስላልቻለ ደግሞም ስለማይችል በመስቀል ላይ ሃጢአታችንን ሊሸከም ፣ሞቶ ሞትን ሊገድል ፣በትንሳኤውም ዘለዓለማዊነታችንን ሊያረጋግጥልን በኩር ሆነልን ።     ስለዚህ የመጣበትን አላማ ስለሚያውቅ ብዙ ውርደት በትህትና ተቀበለ ብዙ ስቃይ በዝምታ አስተናገደ መከራውን ሳይሆን በመከራው የምንተርፈውን የእኛን መዳን እያየ ተፅናና በችንካር እያማጠ ዳግመኛ ከማይጠፋ ዘር  ወለደን።      በሚያስተምርበት ወቅት ይህንን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሶስተኛውም ቀን አነሳዋለሁ እንዳለው ሶስት ቀንና ሶስት ሌሊት በምድር ውስጥ አሳልፎ በሶስተኛው ቀን የሞትን ሃይል አድቅቆ የመቃብርን ህግ ሽሮ ዳግም በማይሞት ማንነት እና አካል በተዘጋ መቃብር ኢየሱስ ተነሳ። ክብር ምስጋና ኃይልና ስልጣን ሁሉ ለእርሱ ይሁን አሜን ።    ውድ አንባቢ ሆይ ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋራ ከተባበርን ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ እርሱን እንመሰለዋለን ሞት የማይቀር እዳ ሆኖ ብንሞትም መነሳታችን ግን አይቀርም በመሬት ላይ የተዘራ የስንዴ ቅንጣት መጀመሪያ ይበሰ...

የፍቅርህ እሳት /ጸሎት/

                 የፍቅርህ እሳት     ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ »   የፍቅርህ እሳት ይነድዳል በየዘመናቱም አዲስ ነውና ሙቀት ያላገኙትን በሃጢአት ቅዝቃዜ በቂምና በበቀል ብርድ የሚንዘፈዘፉትን ነፍሳት በህያው ሙቀቱ ከልብና ከህሊና ሞት ይታደጋል ።     መድሃኒቴ ሆይ » ፍቅር የሚለውን ታላቅ እውነት የተማርኩት ካንተው ነው ። ጥርስ ያወለቀ ጥርሱ እንዲወልቅ አይን ያጠፋ አይኑ እንዲጠፋ በታወጀበት አለም ምህረትና ይቅርታ መውደድና ማፍቀር ሰማእትነት እና ፍጹምነት ከባህሪህ አውጥተህ ስላሳየከኝ ባንተ የነበረው አሳብ በእኔም እንዲኖር ስላበረታከኝ ሁሉን ባንተ ስለተማርኩኝ መውደድን መወደድን ያየሁብህ ወዳጄ አመሰግንሃለው ።     አለሙን አንድ ያደረግከው ሆይ» ላንተ መገዛቴ በሙሉ ሃይሌ እና ጉልበቴ ነው ። ደምህ የሃጢአቴን ብዛት ጠርጎ አስወግዶልኛል ቁስልህ የነፍሴን ቁስል ፈውሶልኛል  ጥምህ የነፍስ ጥሜን ቆርጦልኛል መራብህ የዘለአለም ርሃቤን አስወግዶልኛል የሆንክልኝ ሁሉ ከቃላት በላይ ነው ባወራም ብናገርም ማለቂያ የለውም ።      ሰላሜ ሆይ » የነበረህን ያንን ሁሉ ክብር ትተህ እንደ ምስኪን ደሃ ማደሪያ እንደሌለው መንገደኛ ተንከራትተህ በቤትህ ያሉትን ዘጠና ዘጠኙን ሰራዊትህን ትተህ  በአባትነት ፍለጋህ ያገኘከኝ የማርከኝ የመንግስትህ ዜጋ ያደረከኝ አንተ ለእኔ የዘለአለም መኖሪያዬ ነህ መጠጊያዬና አምባዬ ነህ ።      ውዴ» እንደምወድህ አንተው ታውቃለህ ለእኔ ደስታ እንደደከምክ በድካም እንዳስደስትህ እተጋለሁ የከ...