Posts

Showing posts from March, 2014

ጠላቱን አግኝቶ በመልካም መንግድ የሚሸኝ ማን ነው? by Kesis Tizitaw Samuel /video/

Image
LIQE MEZEMIRAN KESIS TIZITAW SAMUEL.

አስገራሚው የፍቅር ታሪክ

                    አስገራሚው የፍቅር ታሪክ         በመጀመሪያ እግዚአብሄር ሰማይና ምድርን ፈጠረ ስማይና ምድር ሲፈጠሩ አሁን በሰማይና በምድር ውስጥ ያሉት ፍጥረታት በሙሉ በእግዚአብሄር ቃል ሆኑ ፍጥረትን ሁሉ አስቦ በቃሉ የፈጠረው አምላክ በራሱ አርአያ እና አምሳል አዳምን ከአፈር አበጀው የህይወት እስትንፋስን በአፍንጫው እፍ አለበት ህያውም ሆነ የህይወት መመርያ ተሰጠው የተሰጠውን ነጻነት ተጠቅሞ የቀረበለትን ምርጫ ከህይወት አጋሩ ከሄዋን ጋር ተስማምቶ ሞትን መረጠ  የእግዚአብሄርም ቅን ፍርድ በላዩ ወደቀበት ስለዚህ ልጅነቱን ጸጋውን ክብሩን ስልጣኑን ተቀማ  ።         ይህ ታሪካዊ ስህተት የሰው ልጆችን ነጻነት ጠቅልሎ አስሮ በመቃብር የቀበረ የአለማችንን መልክ  የህይወታችንን ውበት በሞት ጥላሸት ለቅልቆ ያበላሸ በመጀመሪያው ንጹህ ታሪካችን ላይ ጠባሳ የጣለ ክስተት ነበር ። በሄዋን ማህጸን በአዳም አብራክ ውስጥ ሆነን ሁላችንም ተረገምን፣የሞትን ፍርድ ተቀበልን ። ቅ/ጳውሎስ ይህንን ሲያብራራ < ስለዚህ ምክንያትሃጢአት  በአንድ ሰው ወደ አለም ገባ በሃጢአትም ሞት እንደዚሁም ሁሉ ሃጢአትን ስለደረጉ ሞት  ለሰው ሁሉ ደረሰ ።> ሮሜ 5፥12 ይህ መጽሃፍ ቅዱሳዊ ቃል እንደሚያስረዳን በዘር እየተላለፈ ትውልድን ሲጨርስ የነበረው ሞት መንስኤው የአዳም በደል እንደሆነ በተጨማሪም ቀጥሎ የተፈጠረው ትውልድም በሃጢአት ባህር ውስጥ የተነከረ ማንነት...

<<< የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም >>>

                 <<<  የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም >>>           ከዚህ በፊት በዚሁ የእግዚአብሄር አሳብ ላይ ባሰፈርኩት ጽሁፍ የተወሰኑ ጉዳዮችን ተመልክተናል ዛሬ ተከታዩን ክፍል እናያለን ። ሶስት መቶ ቀበሮዎችን ሶምሶን ይዞ በጅራታቸው ላይ ችቦ አሰረባቸው እሳት ለኩሶ በጠላት አውድማ ላይ ለቀቃቸው የታሰረባቸውን እሳት ይዘው ሮጡ ተልእኮዋቸውንም ፈጸሙ ። መሳፍንት 15፥4 ሶስት መቶ ሰራዊት ለእልፍ አእላፍ ጠላት ይበቃል ይህ የሚሆነው ግን ተልእኮው እግዚአብሄር ያለበት ሲሆን ነው ። በመሰረቱ እግዚአብሄር በቁጥር ብዛት አያምንም በሶስት መቶ የጌዴዎን ሰራዊት እንደ አንበጣ እስራኤልን የወረረውን መንጋ እንዳልነበረ አድርጎታል መሳፍንት 7፥1-25 ። ወደ አዲስ ኪዳን እውነትም ስንመጣ ህይወታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለወንጌል አገልግሎት የመረጠው 12ቱን ሃዋርያት ነበረ ከእነርሱም ጋር የተደመሩት 120 የወንጌል እና የአዲስ ኪዳን ቤተሰብ ብቻ ነበሩ ። ዛሬ አለምን የከደነው ወንጌል በነዚህ ጥቂት ሰዎች አገልግሎት  ተጀምሮ ነው ለሁላችን የተረፈው ። በጥቂቶች ብዙ መስራት ለሚችል የሃይሉ እና የጥበቡ ብዛት ለማይለካ ለእግዚአብሄር ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ክብር ይሁን አሜን ።                   የዛሬዋም የከርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ኢያሱስ የጣለባትን የወንጌል አደራ በአግባቡ እንዳትወጣ የወንጌሉንም አላማ የጨበጡ  አገልጋዮች ለመንገዱ በተፈቀደው ፍጥነት ሮጠው ወንጌልን እንዳ...

የእግዚአብሄር ቃል አይታሰርም 1

                የእግዚአብሄር ቃል አይታሰርም            ክልከላ አልፎ የሚሰማ አዋጅ አልፎ የሚሰራ ከባለስልጣናት በላይ ባለስልጣን የሆነው መለኮታዊው የእግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው። ቀድመው የተነሱ መንግስታት ያወጡትን ህግ ቀጥሎ የተነሱት በሚመቻቸው መንገድ እየቀለበሱ ቀይረውታል ፣ በዘመናችን ደግሞ አንድ አስገራሚ ክስተት አለ ይኸውም ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት የሚባለው ለተወሰኑ ሃያላን ሃገራት የተሰጠ መብት ነው ። ሁኔታው ዘመናዊ የሚመስል ቢሆንም ከፍትሃዊነት አንጻር ብዙ አከራካሪ ነጥቦችን ማስነሳቱ አልቀረም ።በመሰረቱ የእኔ ነጥብ ምድራዊ ህግ ማብራራት ሳይሆን በምድራዊ ህግ እና በምድራዊ ባለስልጣናት የማይታሰረውን ሰማያዊ ቃል መመስከር ነው ። ስለዚህ አምላካችን እግዚአብሔር በድምጽ የማይሻር ድምጽ ፣ በምድራዊ ህግ የማይቀለበስ ህግ፣ የሰላ አንደበት ባላቸው ፈላስፎች ቃል የማይረታ ቃል ያለው ንጉስ ነው ። እኛም የምንመራው በዚህ የህይወት ቃል ስለሆነ ስለዚህ ስልጣን ስላለው ቃል ለነፍሴና ለነፍሳችሁ ለልቤና ለልባችሁ ልጽፍ ወደድኩ።     በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው የክርስትና ህይወት ጉልበታምና  በድንቆች የታጀበ ነበረ ፤ መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የመሰረታት ቤተክርስቲያን ዛሬ ያላትን ነጻነት አግኝታ ከማየታችን በፊት ብዙ መከራዎችን አልፋለች ቤተ ክርስቲያን ስንል የክርስቲያኖችን ህብረት ማለታችን ነው ። ለተቀበሉት የወንጌል አደራ ሲሉ አንገታቸውን ለሰይፍ ሰውነታቸ...

አሸናፊ ነህ /ግጥም/

Image

እንዴት እንጹም ከባለፈው የቀጠለ፥

                       እንዴት እንጹም  ከባለፈው የቀጠለ፥ 4/ከጸሎት ጋር ፥            ውድ አንባብያን በዚህ የእኛ ልዩ እድል በሆነው  የጌታችን ጾም ውስጥ እያንዳንዳችን ከሰማይ መልስ የሚጠብቁ የግል ጥያቄዎች አሉን እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ላንሳ ስንቶቻችን ሃይምኖታዊ {ክርስቲያናዊ} እና ሃገራዊ ጥያቄዎች ይዘን በጌታ ፊት ቆመናል የክርስቶስ ፍቅር ልቡን ያሳረፈለት የተደላደለ መንፈሳዊ አቛም ያለው ሰው ከግል ጥያቄው እኩል ስለ ሃይማኖቱ ሰላም ስለ ወንድሞቹ እና እህቶቹ የህይወት ስኬት ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት አልፎ ተርፎ ስለ ዓለም ሁሉ ይጸልያል ። ክርስትና ሲያድግ ልብ ይሰፋል በሰፊ ልቡ ደግሞ መታሰብ ያለባቸው ጠቅላላ ጉዳዮችን በጾሙም በጸሎቱም ክበቡን ሳያጠብብ ሁሉን ያስባል ። ከዚህ እውነት በመነሳት የራሳችንን ህይወት እንድንዳስስ አሳስባለሁ ።       ጾም እና ጸሎት በንግግር ውበት ብቻ ሳይሆን  በአንድምታም ፤ በክርስትና መርህም የማይነጣጠሉ የአምልኮ ስርአቶች ናቸው ። በመሰረቱ ጾማችን መጾም ስላለብን እና በአዋጅ ሁሉም ስለ ጾመ በልምድ  መሆን የለበትም በዓላማ በአጀንዳ ማለትም በጾሙ መጨረሻ ከጌታ ደጋግ መዳፎች አንድ የምንቀበለው ነገር እንዲኖር በቆረጠ መንፈስ በዝግጅት ልንጾም ይገባል ...

እንዴት እንጹም ?

                            እንዴት እንጹም ? ጾማችን የሚጠበቅበትን ውጤትማምጣት እንዲችል የሚከተሉት የቅድስና ተግባራት አብረውት ሊከናወኑ ይገባል ፤ 1/ ከንቱ ውዳሴ የሌለበት ሊሆን ይገባል ፦ ጌታችን በወንጌል ማቴ 6፥16 ስትጦሙም እንደ ግብዞች አትጠውልጉ ለሰዎች     እንደu ጡዋሚ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና እውነት እውነት እላቹሃለው ዋጋቸውን ተቀብለዋል ። ይህ ማለት ዋጋ ከሰማይ     የማያመጣ ከንቱ የሆነ  ድካም ነው ።ስለዚህ የጾማችን አላማ የሰዎችን ትኩርት መሳብሳይሆን የአምላካችንን ምህረት መውረስ     ሊሆን ይገባል። 2/በፍቅርና በአንድነት፦ የቤተ ክርስቲያናችን የዜማ ሰው ቅ/ያሬድ <ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ ወንትፋቀር በበይናቲነ> ማለት-    ጾምን እንጹም ወንድማችንን እንውደድ እርስ በእርሳችንም እንዋደድ።በማለት ጾም ከፍቅር ጋር ወንድምን ከመውደጋር ሊሆን         እንደሚገባ ይናገራል።የተወደዳችሁ ክርስቲያኖች ያለ ፍቅር የቱንም ያህል በእያንዳንዱ አገልግሎት ብንሰማራ                    ...