TIZITAW SAMUEL
አስገራሚው የፍቅር ታሪክ
አስገራሚው የፍቅር ታሪክ በመጀመሪያ እግዚአብሄር ሰማይና ምድርን ፈጠረ ስማይና ምድር ሲፈጠሩ አሁን በሰማይና በምድር ውስጥ ያሉት ፍጥረታት በሙሉ በእግዚአብሄር ቃል ሆኑ ፍጥረትን ሁሉ አስቦ በቃሉ የፈጠረው አምላክ በራሱ አርአያ እና አምሳል አዳምን ከአፈር አበጀው የህይወት እስትንፋስን በአፍንጫው እፍ አለበት ህያውም ሆነ የህይወት መመርያ ተሰጠው የተሰጠውን ነጻነት ተጠቅሞ የቀረበለትን ምርጫ ከህይወት አጋሩ ከሄዋን ጋር ተስማምቶ ሞትን መረጠ የእግዚአብሄርም ቅን ፍርድ በላዩ ወደቀበት ስለዚህ ልጅነቱን ጸጋውን ክብሩን ስልጣኑን ተቀማ ። ይህ ታሪካዊ ስህተት የሰው ልጆችን ነጻነት ጠቅልሎ አስሮ በመቃብር የቀበረ የአለማችንን መልክ የህይወታችንን ውበት በሞት ጥላሸት ለቅልቆ ያበላሸ በመጀመሪያው ንጹህ ታሪካችን ላይ ጠባሳ የጣለ ክስተት ነበር ። በሄዋን ማህጸን በአዳም አብራክ ውስጥ ሆነን ሁላችንም ተረገምን፣የሞትን ፍርድ ተቀበልን ። ቅ/ጳውሎስ ይህንን ሲያብራራ < ስለዚህ ምክንያትሃጢአት በአንድ ሰው ወደ አለም ገባ በሃጢአትም ሞት እንደዚሁም ሁሉ ሃጢአትን ስለደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ ።> ሮሜ 5፥12 ይህ መጽሃፍ ቅዱሳዊ ቃል እንደሚያስረዳን በዘር እየተላለፈ ትውልድን ሲጨርስ የነበረው ሞት መንስኤው የአዳም በደል እንደሆነ በተጨማሪም ቀጥሎ የተፈጠረው ትውልድም በሃጢአት ባህር ውስጥ የተነከረ ማንነት...