እናንብብ

<< እናንብብ>>
በህይወቴ ሁሉ እኔ ትዝ የሚለኝ
ህጻን ሳለሁ ግና አባቴ የነገረኝ
<እንዃን በእጅህ ያለ መጽሃፍ 
የወደቀ ወረቀት ሳታነብብ አትለፍ>
ደጋግሞ የነገረኝ ይሄ ታላቅ ምክር 
ነቃቅሎ ጥሎታል የስንፍናዬን ጦር
ስለዚህ አነብባለሁ እመረምራለሁ
እንኳን በእጄ ካለው ከአዲሱ መጽሐፍ 
ወድቆ ካገኘሁት ብዙ ተምሬአለሁ።
     ትዝታው ሳሙኤል።

Popular posts from this blog

እንዴት እንጹም ?

አስገራሚው የፍቅር ታሪክ