ጸሎት ጸሎት ማለት ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር ማለት ነው ። በጸሎት የምንፈልገውን ነገር ሁሉ ከጌታ ዘንድ መጠየቅ እና ማግኘት እንችላለን ። ከጸሃይ በታች ያለው ህይወታችን ጉድለት የበዛበት ሙሉ ሆኖ የማያውቅ ሙሉ መሆን የማይችል ቀዳዳ ነው ። በመሰረቱ ህይወት ጎዶሎ የሚሆነው ከምኞታችን አንጻር እንጂ ያለኝ ይበቃኛል ለሚል ሰው ጉድለቱን ሳይሆን ሁል ጊዜ የሚያየው ሙላቱን ነው ስለዚህ በምስጋና የተሞላ ማንነት አለው ። በመሰረቱ አብዝቶ ከሚጸልይ ይልቅ አብዝቶ የሚያመሰግን ሰው ብዙ በረከት ይቀበላል , መጽሃፍ ቅዱስ እንዳርጋገጠልን ጌታም እንዳስተማረው በቅድሚያ መንግስቱንና ጽድቁን ፈልጉ ሌላው ሁሉ ይጨመርላችሃል ማቴ 6፥33 እንዳለው እኛ ለቃሉ በተገዛ ማንነት የዘላለም መኖሪያ የሆነችውን ርስታችንን መንግስተ ሰማያትን ለመውረስ ጽድቅ በተባለው እውነት በኢየሱስ ክርስቶስ ለመዳን ብቻ ነው በጽኑ ማሰብ እና መፈለግ ያለብን ። በዚህ የጸሎት አቅጣጫ እስከዛሬ የዘለቅንበትን የጸሎት ህይወት ለመገምገም እንሞክራለን , በጉድለት የተሞላውን ማንነታችንን በቃኝ የማያውቀው ፍላጎታችንን እንዲሁም ልጛም የሌለው የምኞት ፈረሳችንን ከአንድ ምእራፍ ለማሳረፍ ትልቁ መፍትሄ ጸሎት ነው ። በጸሎት ፈጣሪን ተማጽነው ጠላታቸውን የረቱ ፣ ከመካንነት ነቀፋ ተገላግለው በልጅ የተባረኩ ፣ ከሰው ያሳነሳቸውን አንገታቸውን ያስደፋቸውን መብላት እየፈለጉ እንዳይበሉ...