Posts

Showing posts from February, 2015

አስተርእዮ

                        አስተርእዮ      «የዲያብሎስን ስራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ለጅ ተገለጠ»1ኛ ዮሐ3፥8 አስተርእዮ ማለት በአጭር ቃል መገለጥ ማለት ነው ። የማይታየው አምላክ(የመለኮት ባህሪ የስጋን ባህሪ ገንዘቡ አድርጎ በተዋህዶ ሲያከብረን) ሥጋ ለብሶ ታየ ተገለጠ፣የማይራበው ተራበ፣የማይጠማው ተጠማ፣ የማይዳሰሰው ተዳሰሰ፣የማይረታው ተረታ፣የማይደፈረው ተደፈረ ፣የማይሞተው ሞተ በዚህም ሁሉ ድንቅ ስራ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ ያለው ልዩ ፍቅር ተገለጠ ታየ ታወቀ <አስተርእዮ>።        በዮርዳኖስ ወንዝ ዳር ጌታ በሎሌው እጅ ከተጠመቀ በኋላ ከውሃው ሲወጣ መንፈስ ቅዱሰ  በርግብ አምሳል ከማደሪያው መጥቶ በኢየሱሰ  አናት ላይ አረፈ አብ ደግሞ በነጎድጓድ ድምፁ እያስተጋባ እያንጎደጎደ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት ሲል ተደመጠ ፣የአብ አባትነት ፣የወልድ ልጅነት፣ የመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት በልዩ ግርማና ክብር ተገለጠ የፈቃድ አንድነት እና የአካል ሶስትነት ተገለጠ።ማቴዎስ 3፥1-ፍጻሜ።        ክርስትና የተገለጠ የመገለጥ ሃይማኖት ነው ። የምናምነው በተገለጠው ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው ያዳነንም በህዝብና በአህዛብ ፊት በተገለጠው ፍቅሩ ነው ።ዮሐንስ በወንጌሉ «እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው »ዮሐ 1፥18 በተደጋጋሚ አባቴ እያለ ስለ አባቱ አጽናኙ እያለ መንፈስ ቅዱስን የተረከልን የሰማዩን ምስጢር ያስተማረን የተረከልን ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። ለአምል...