መንገድ እውነት ሕይወት ዮሐ 14፥6
መንገድ እውነት ሕይወት ዮሐንስ 14÷6 ውድ የዚህ መንፈሳዊ ድህረ ገፅ አንባቢዎች እንደምን ከርማችኋል የጌታ ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ በዚህ ፅሁፍ ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን ሶስት ታላላቅ ቃላቶች በተራ ትርጉማቸውን እያየን የመድሃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ታላቅ የማዳን ስራ እንመሰክራለን ። የዚህ አለም የኢኮኖሚ ተንታኞች ለአንዲት አገር ፈጣን እድገት እና ልማት ትልቁን ድርሻ የሚወስደው መንገድ እንደሆነ ይስማማሉ ። በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ክፍላተ ሃገራትን እንዲሁም ከአዋሳኝ አገራት ጋር የንግድ የባሕል የኢኮኖሚ ልውውጦችን ለማድረግ ጉልህ ድርሻ የሚወጣው መንገድ እንደሆነ ያረጋግጣሉ ሃሳቡ ከእውነት ያልራቀ ስለሆነ እኛንም ያሳምነናል ። በሃይማኖታዊ እይታም መሰረት መንገድ ብዙ ሚስጥራትን የያዘ ቃል ነው ስለዚህ የዚህ ዓለም ጠበብቶች የተስማሙበትን የመንገድን አስፈላጊነት ማለትም በድንጋይ ወይም ዘመናዊው አስፋልት አልያም የጥርጊያ መንገድ ሁሉም እንደየአቅማቸው ለህብረተሰቡ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ከግምት ውስጥ በማስገባት እኛ ልንለው የምንችለውን ፈርጥ እውነት ከፍ አድርገን እናሳያለን ። ...